I am not a diaspora

Posted on : August 14, 2018 | post in : ESAN FOUNDER |Comments Off on I am not a diaspora |

ይድረስ ለኢትዮጵያ ፖለቲካ መሪዎች በያላችሁበት እንደምን ውላችሁ አድራችኋል  አኔ ከኢትዮጵያ ሐገሬ ሓሳብና ናፍቆት በስተቀር ደህና ነኝ የዚህ መልክት ዋናው ጉዳይ  “ኢትዮጵያ ያለቸው ኢትዮጵያውያን ባሉበት ቦታ ሁሉ ነው” የሚባለውን ጽንሰ ሕሳብ ላተገነዘቡ ወግኖች ለማስተማር ነው–

ይሄ እንዴት ይሆናል ?  እግዜር የሰጣት ዕድል ሆኖ ኢትዮጵያ በብዙ ሐግሮች ደርጅተው የሚኖሩ ልጆች አሏት እነዚህ ልጆች ኢትዮጵያ ተብላ ከምትጠራው ሐገራቸውና ወገኖቻቸው በምንም መልኩ አይለዩም የግዜና የአጋጣሚ ጉዳይ ሆኖ በቦታ ተራርቀው ይኑሩ እንጂ አነዚህ ሁለት ክፍሎች በመክልም በሓሳብም በአስተሳሰብም በአምነትም አንድ ናቸው እንደውም ከዋናይቱ ኢትዮጵያ  በቦታ ራቅ ብለው የሚኖሩት የኢትዮጵያን ይዞታ አሰፉት በሰላም ኃይል ሳያነሱ የኢቶጵያን መንፈስ በዓለም አስፋፉት- ቤት ንብረት ይዘዋል ስልጣን ይዘዋል- የአማርኛ የግ ዕዝ የትግርኛ ወዘተ ቋንቋዎች በብዙ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርት ይሰጣል- የኢትዮጵያ እምነት ተቋማት ኢትዮጵያውያን ባሉበት ሁሉ አሉ የኢትዮጵያ ንግድ ተፋፍቷል ኢትዮጵያውያን በትምህርታቸውና በስራቸው አንደኛ እየሆኑ ነው ሐገራቸውንና የሐገራቸውን ወጣት ከማንኛውም በዓለም ካለ ወጣት እኩል ለማድረግ እየጣሩ ነው -በኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ በብዙ መንግድ በቀጥታ በኢኮኖሚ እየተሳተፉ ነው በዛላይ ደግሞ በብዙ ቢሊዮን የሚቆጠር ጥሬ ገንዘብ በቀጥታ ለኢትዮጵያ ወጎኖቻቸው ይሰጣሉ ይሄ ሁሉ ነገር እየተደረገ ይሄንን ሕብረተሰው ዲያስፖራ እያሉ መጥራት በፍጹም ትክክል አይደለም -ዲያስፖራ የሚለው ቃል እንደ ልማድ ይሆንና ተጠሪውን ማግለል ይጀመራል -እንደ ጎሳ ሆኖ ቁጭ ይላል-

ባሁኑ ግዜ እናንተ ያለባችሁ ትልቁ ችግር ሕዝቡን በሐይማኖትና በጎሳ ተከፋፍሉ ለብዙ አመታት እንዲኖር ስላደረጋችሁት ባሁኑ ግዜ አንዱ አንዱን አያምንም የሰው አስተሳሰብ ተወላግዷል ተበላሽቷል ሰውን ሰው ከማለት ጎሳ ማለት ይቀለዋል – አሁን ባለው ሁኔታ አንድ ሰው እንኳን ሲሾም የትኛው ጎሳ የትኛው ሐይማኖት እንደተሾመ ለማወቅ ጥረት ይደረጋል- የተሾመው ሰው ነው እንጂ ጎሳ አይደለም-

በኢትዮጵያ ባለማወቅ የፋሺስት አስተሳሰብ እየዳበረ ነው -ላይ ላዩ ደህና ይመስላል ውስጡ ግን መርዝ አለ – መርዙን እያየነው ነው – ሁሉን ነገር ተውት – አሁን ለምሳሌ አንድ ልጅ በሚማርበት ትምህርት ቤት በጎሳ ምክንያት ከተጉላላ ወይም አደጋ ከደረሰበት የምታራምዱት ስር ዓት ሕብረተስቡን አበላሽቶታል ማለት ነው – ለያንዳንዱ ሰው ጠባቂ ማቆም አይቻልም – ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ቦታ ሄጃለሁ አልፎ አልፎ ፖሊስ ይታያል ሕብረተሰብ ራሱን እየጠበቀ ስለሆነ ነው.- አያችሁ ሕብረተሰብ ራሱን የቻለ ዳኛ ነው ያልተበላሽ ሕብረተሰብ ጥሩ ዳኝነት ይሰጣል ሁለት ሰዎች ሲጣሉ የምንም ጎሳ ቢሆኑም ይገላግላል ያስታርቃል- የተበላሸ መረን የተለቀቀ ሕብረተሰብ ግን ሁለት ሰዎች ቢጣሉ ሁለት ጎሳዎች እንደተጣሉ ያይና የርስ በርስ ጦርነት በሐሳቡ ይጀምራል ፖለቲከኞች ከደገፉት ደግሞ ሕዝብን ያፈናቅላል-ይሄ ተደርጓል

ይቺን አስታውሱ ልክ በስነ ሥርዓት ያላደገ ልጅ እንደሚበላሽ ሁሉ ትክክለኛ ስነ ሥርዓት ያለተሰጠው ህብረተትሰብ ይበላሻል ሰውን ሰው ብሎ መጥራት ያቆማል -ይቺን አትርሱ፡ ሰው ሰው መሆኑን ካላመነ ሌላውን ሰው እንደ አውሬ አድኖ ሊበላው ይችላል -ብይበላውም ሊያጠፋው ይችላል-ይሄ ተደርጓል – ካሙዙ ባንዳ የሚባል መሪ ሰው በልቷል -የሩዋንዳን የሰርቢያን የቱርክን የጀርመንን ታሪክ አንብቡ -የተበላሸ ህብረተሰብ ምን ማድረግ እንደሚችል ማወቅ ትችላላችሁ -በዚህ ዓይነት ሲታይ ዳያስፖራ የሚለው አጠራር የተጠሪውን ሰውነት ይቀንሳል -ሕብረተስብን አታወናብዱት አታበላሹት ሰው ሰው መሆኡን አስተምሩት

ዲያስፖራ የሚለው አጠራር እኔ አካባቢ ብሎክ ተደርጓል- ብሎክ እዳለደርጋችሁ ይሄን ቃል እንዳትጠቀሙ (ለፈግግታያክል)

Comments are closed.
Theme Designed Bymarksitbd