Message to Students

Posted on : August 14, 2018 | post in : General Knowledge |Comments Off on Message to Students |

ለኢትዮጵያ ተማሪዎች በሙሉ ከአቶ አበበ ከበደ

እንድምን ውላችሁ አድራችኋል እኔ ቸሩ አምላካችን ይመስገን ደህና ነኝ – ይህንን መልክት በጥሞና አንብቡት-ባሁኑ ጊዜ በሃግራችን ብዙ ከባድ ስራዎች አሉ አናንተ ትምህርታችሁን ስትምሩ ለነዚህ ከባድ ስራዎች የሚኖራችሁን ሚና በማሰብ መሆን አለበት ይህን ልታደርጉ የምትችሉት እናንተ በ ሰውናታችሁና በአ ዕምሯችሁ ስትጎለብቱ ነው ስለዚህ ከሚክተሉት አደጋ ሊጥሏችህ ከሚችሉ ነገሮች አደርጉ ወይም ተቆጠቡ (ለሴቶችም ለውንዶችም)
  1. ጓደኛህን ከራስህ በላይ አክብረው
  2. ጎሳን ሃይማኖትን የሚመለከቱ ሙግት ውስጥ አትግባ
  3. ስውነትህንና አዕምሮህን ከሚጎዱ ነገሮች ተቆጠብ ጫት አትቃም ሲጃራ አታጭስ
  4. ሰውነትህን በስፖርት አዳብር
  5. ሴቶችን አትድፈር እንደ እህትህ እንደናትህ አክብራቸው
  6. ከጥናትና ከጫወታ የተረፍ ጊዜህን በበጎ ፈቃደኝነት አሳልፈው
  7. በጥናትህ ትጋ አንብብ አንብብ መርምር አጣራ
  8. ሃሳብህ ከፍተኛ ትምህርት መማር ከሆነ ማርክህ ከ 3.5 በላይ መሆን አለበት ስለዚህ ማንኛውንም ኮርስ ቢሰለችህም በደንብ አጥንተህ ኤ ማግኘት አለብህ
  9. ምክር ሲአስፈልግህ ምክር ከሚገኝበት ከቅርብ ዘመድ ከምታምነው ጓደኛ ጠይቅ
  10. አሉባልታ ውስጥ ምንም ለውጥ የማታመጣበት ጉዳይ ውስጥ አትግባ
  11. ፌስ ቡክህ ውስጥ የማታቀውን ሰው አታስገባ ወስላታ ሾካካ አድመኛ አኳኋን ካለው ሰው ሽሽ እንደዚህ አይነት ጓደና ካደረግህ ኤፍቢአይ ኢንተርፖል የሚባለው ሁሉ ይከታተልሃል – ይሄ ቀልድ አደለም ተጠንቀቅ
  12. የምነት ሰው ከሆንክ እምነትህን አጠንክር ግን ያንተ ሃይማኖት ከማንም እንደባይበልጥ እወቅ
ይሄ በዚህ እንዳለ በተየ የኔ የየአቶ አበበ ከበደ ጓደኛ ከሆንክ የምትሰራውን እከታተላለሁ ብዙ ስራ አለብህ ግዜ ሲኖርህ አበበ ምን ብሏል እያልክ የምጽፈውን ተከታተል አንተ ያኢትዮጵያ ልጅ ስለሆንክ በኢትዮጵያ ጉዳይ ፋታ የለም — ዐሁን በቃ ስራህን ጅምር ወንድማችሁና አክባሪአችሁ አበበ ከበደ፣ ብሄረ አትዮጵያ ኩሽ ወአርሲ ጭላሎ አውራጃ

ኡኡኡ የንጉስ ያለህ፡

አይ የኔ ወገኖች መቼ ነው የምትማሩት ? እስቲ አካባቢያችሁ የሚሆነውን እዩት – አሁን ከሃምሌ ጀምሮ አሜሪካኖች አንዴ በሰደድ እሳት እንዴ በአውሎ ንፋስ እየተደበደቡ ነው ልብ ብላችሁ ይህንን እዩ- ይህንን ቁጣ ለመከላከልና በሱ ሳቢያ የጠፋውን ንብረት ለመተካት የተጎዳውን ህዝባቸውን መልሶ ለማቋቁም የሚያደርጉትን ጥረት እዩ – ከህፃን ልጅ አንስቶ እስከ ሽማግሌ -ከደሃ አንስቶ እስከ ሃብታም- ከትንሽ ድርጅት አንስቶ እስክ ትልቁ ድርጅት- ሲረባርቡ ታያላችሁ- ኢትዮጵያ ውስጥ ልክ እንደነሱ ያሉ ችግሮች ሞልተዋል ረሃብ ድህንት በሽታ የውሃ እጥረት የአካባቢ መውደም የትምርት ቤቶች መደህየት ምን አለፋችሁ እትዮጵያና ህዝቦቿ ለአመታት ከትውልድ ትውልድ እየላሸቀች ነው -ርብርቡ የታል ? USAID ና የተባበሩት መንግስታት መፍትሄ እንዲሰጡ ነው የምትጠብቁት ? ውስኪ እንደዉሃ ይጠጣል ከፓሪስ ከአዲስ አበባ ክትፎ ይታዘዛል ማርሴዲስ ይነዳል ብር እንደዉሃ ይፈሳል ለልደት ድል ያለ ድግስ ይደገሳል አዲስ አበባ አራዳ ወጥታችሁ ጉድ እዩ- ዲሲ ሄዳችሁ ፓሪስ ሄዳችህ ጉዳችሁን እዩ- ችግርን ለማስወገድ ርብርቡ የታል ? ችግር ዛሬ ከልተፈታ ነገ ሁለት እጥፍ ይሆናል ተነገ ወዲያ አራት እጥፍ ይሆናል -ዝም ብሎ USAID ና የተባበሩት መንግስታት አይጠበቁም – ከአንድ ቀን በፊት ስለ መጽሃፍ ጉዳይ ሃሳብ ልውውጥ ላይ አንደ ወዳጅ USAID ሄደህ አመልክት አለኝ- ሳስበው እኔ ምን ሆኜ ነው USAID ሄጄ አቤት የምልበት ምክንያት ? እጄ ተቆርጧል የአዕምሮ በሽታ አለብኝ ? እሱስ ቢሆን ምን ሆኗል ? ኢትዮጵያ የሚባል ራሱን የቻለ ሕብረተ ስብ አለ -ይሄ ሕብረተሰብ ፋይዳ የሌለው ዋጋ የሌለው ቡቱቶ ለባሽ በሽተኛ ለማኝ ነው ማለት ነው ? በዚህ ምክንያት ያልተወለደውን ገዳዩን ፈረንጅ በእምብርክኩ እየሄደ መለመን አለበት ማለት ነው ? ይሄ ኢትዮጵያዊ አበበ ከበደ የሚባለው እያለ አይሆንም አንለምንም የውጭ እርዳታ ራሳችን እናበጀዋለን -በየሰፈሩ በየጓዳው በየስራቻው ቁጭ ብለን ይህ ይሆናል ያ አይሆንም እያልን ግዜ የምናባክን ሰዎች ተነስትን መስራት አለብን -ልንሰራ የምንችላቸውን ትናንሽ ነገሮች እየመረጥን መስራት እንደየስራው አይነት ራሳችንን ማሰባሰብ ሃሳብ ተቀያየሮ ስራ ላይ ሊውሉ የሚችሉ ነግሮችን መርጦ ስራ ላይ ማዋል – ወሬ በቃ- ከዚህ ጽሁፍ ቀጥሎ ልንሳተፍባቸው የምንችል ውጥኖች ይቀርባሉ የሚስማማችሁን እየመረጣችሁ እርዳታችሁን ለግሱ – እነዚህን ውጥኖች ለምታውቋቸው ሁሉ አስተላልፉ– በትዕግስት ከተሰራ ሁሉም ይሳካል —— ይህ ጽሁፍ ለኢትዮጵያውያን ብቻ ነው የተጻፈው በአማርኛ ነው አማርኛን የሚናገሩ ኢትዮጵያውያን ብቻ ናቸው —ሚስጥር ነው – አማርኛ የማይችል ካለ በጉግል ተርጉም በሉት
Comments are closed.
Theme Designed Bymarksitbd