Message

Posted on : June 3, 2019 | post in : General Knowledge |Comments Off on Message |

ለኢትዮጵያ ትምህርት ተቋማት አስተዳዳሪዎች ና አስተማሪዎች በሙሉ

ስሜ አቶ አበበ ከበደ ይባላል እንደምን ውላችሁ አድራችኋል እኔ ቸሩ እግዚአብሄር የመስገን ደህና ነኝ-መቼም አንድ ሰው ዳርቆሞ ምንም ያህል በማያወቀው ጉዳይ መለእክት ሲያስተላልፍ አስተያየት ሲሰጥ ትንሽ አግባብ ያለው አይመስልም በተለይ ደግሞ ለአናንተ ወንድሞቼና እህቶቼ በቀጥታ በግንባር የአደራ ልጆቻችሁ ና ተማሪዎቻችህ በሰላምና በደስታ ስነምግባር የተሞላበት ትምህርት ለምትሰጡ ይህንን ልቤ ላይ የሚቀዋለውን ስጋት ማካፈል አስፈላጊነቱ ስለታየኝ ይህንን መልክት እንድትቀበሉኝ በትህትና እለምናችኋለሁ-

አኔ ወድማቸው ያደኩት የምኖርበት ዕድሜዬን ሙሉ ትምህርት ቤት ነው ከዚህም ዓለም ስሄድ መነሻዬ ከትምህርት ቤት ውስጥ እንዲሆን ጸሎቴ ነው ምንም ዓይነት የስነ ልቦና ትምህርት የለኝም ከልምድ ተማሪን ከማየት ተማሪ ምን እንደሚሰማው እገምታለሁ

አባት እናት ልጁን ለእናንተ ሲስጥ ሲያጠፋ ግስጹልኝ አስተምርሩልኝ ሰው አድርጉልኝ አደራ ብሎ አስረክቧችኋል እናንተም በትጋት አለምንም ማወላወል ልጁን ተረክባችሁ አደራችሁን እየተወጣችሁ ነው

ወንድሞቼና እህቶቼ

እናንተና እኔ እንደምናውቀው ትምህርት ቤትና አስተማሪ ወሰን የለውም አላማው አንድ ነው የዓለም ዜጋን በዕውቀት አንጾ ተማሪው በዚች ምድር በሄደበት ቦታ ሁሉ ካምሳያው ሰው ጋር አብሮ ሊኖር የሚችል ማለት ነው-አብሮ መኖር ማለት እንደባይተዋር ዳርቆሞ የሚያይ ሳይሆን ካምሳያዎቹ ጋር እየተባበረ ለህብረተስብ ና ለዓለም ችግሮች መፍትሄ የሚስጥ አገላብጦ የሚስራ ዜጋ ሆነ ማለት ነው -እናንተ ያስተማራችኋቸው -አንዱም እኔ ነኝ- በተራችን ልክ እናንተ እንዳስተማራችሁን የዓለምን ወጣት በዕውቀት እያነጽን ለዓለም እያስረከብን ነው በዚህ ምክንያት አስተማሪ ወሰን የለውም ስራው የትም ተሰራ የትም በአስተማሪና በትጋት በሚሰራ ተማሪ ምክንያት ዓለም እያደገች ነው

ተማሪዎች ነገር ቶሎ የሚይዙ ደግሞ ለያዙት ነገር ችኩል ሃሳብ የሚሰነዝሩ ናቸው- ሳይንስ እንደሚያሳየው አንጎል 25 ዓመት ያክል እንሰከሚሞላው የሚያግድ አካል ነው- እናንተ የምስታስተምሯቸው በብዛት እድሚያቸው ከ 5 አመት እስከ 25 ዓመት ነው ስለዚህ በማንኛውም ሁኔታ እነዚህ ልጆች ላይ የአዕምሮ ጫና እንዳይኖር ሌት ተቀን መስራት ያስፈልጋል 

እንግዲህ አገራችን ኢትዮጵያ ላይ ያንዣበበው ሁኔታ ተማሪዎችን የአዕምሮ ረፍት ይነሳል -ስለዚህ ልጆችን በተናጠልም ሆነ በቡድን ምክር መስጠት ከትምህርት ቤት ውጭ የተደረገ ከፋ ያለ ነገር የነሱ ስህተት እንዳልሆነ እንዲያምኑ ማድረግ ያስፈልጋል 

በየቀኑ የአብሮ መኖር ዘዴን ማስተማር የበጎ ፈቃደኝነትን ምግባር በስራ እንዲያውቁት ማድረግ -አንተ ትብስ አንቺ ትብሽ መባባል የትምህርቱን ዋና መሰረት ማድረግ -ተማሪው ትምህርት ቤቱን እንደ ሁለተኛ ቤቱ እንድያየው ማሳመን ያሰፈልጋል

ውጭ ባለው ስሜት ተንሳስተው እንዳይጣሉ ማድረግ-እርስበርስ እንዳይላከፉ ማድረግ -ልጆች ከተጣሉ እርስበርሳቸው እንዲሸመጋገሉ ማድረግ -ልጁ ትንሽ ካስቸገረ ፖሊስ አስመጥቶ ልጁን ወደ እንግልት ከመውሰድ በፊት ቤተስብን ማነጋገር -ረጋ እስከሚል ትምህርት ቤት እንዳይመጣ ማድረግ- ልጆች ጎሳቸውን በሚመለከት ሃይለኛ ሃሳብ ቢለዋወጡና ትግል ቢገጥሙ ጥፋተኛው ቢታወቅም ሁለቱንም መገሰጽ ነው- እዛ ከመድረሳቸው በፊት ግን የሃሳብ ልዩነት ጥሩ መሆኑን አብሮ ለመኖር ሁልግዜ መስማማት አስፈላጊ እንዳልሆነ እንዲያውቁ ማደረግ- የመደራደርና የሙግት ዘዴ ማስተማር ያስፈልጋል

ባሁኑ ግዜ ልጆቹ ከመደበኛው ትምህርት ሌላ ከአካባቢያቸውና በኢተርኔት ጥሩም ሆነ አወናባጅ ትምህርት እየቀሰሙ ነው -ልጆች ብስሉን ከቀሊሉ እንዲለዩ የሚስችላቸው ዕውቀት መስጠት በጣም አሰፈላጊ ነው 

-ስራው ብዙ ነው ሁላችንም በያለንበት የዓለምን ዜጋ በማነጽ ላይ ያለን ሰዎች አብረን እንሰራለን – ያሉትን ችግሮች እየተመካከርን እንፈታለን 

እኔ ወድማቸህ የምኖረው ለተማሪና ለሚማርበት ትምህርት ቤት ነው -አሰፈላጊ በሆነው ነገር ሁሉ እንተጋገዛለን -የአስተማሪዎችና የትምህርት አስተዳዳሪዎች አብሮ መስራት ከመቼውም ይበልጥ አሁን ነው —

ወድሞቼና እህቶቼ እኔ ከናንተ በላይ አለውቅም በዚህ ምክንያት ከላይ የነገርኳችሁን አንድ የቤተሰብ አባት እንደጻፈው ቁጠሩልኝ 

በርቱ- ነገ ጸሃይ እንደ ልማዷ ትወጣለች ነገ ጥሩ ቀን ይሆናል

ወንድማችሁና አክባሪያችሁ

አቶ አበበ ከበደ

Comments are closed.
Theme Designed Bymarksitbd