Ethiopian Periodic Table
Chemistry Just for smile sake-by Abebe Kebede
ህይድሮጅን ስሙ የመጣው እንደዚህ ነው ΰδωρ (hydōr) = water + γεινομαι (geinomai) = to engender, bring forth⇒ bringing forth water (Greek), named by Antoine Lavoisier in 1793–
እኔ ሳስበው ህይድሮጅን የሚለውን ህዝቡ እንዲገባው ብተረጉመው “የውሃ ብቅል” “በቅለውሃ” “የውሃ ዘር” “ዘረውሃ” እንደ ግዕዝ ደግሞ
“ብቅለማይ” “ዘረማይ” ብዬ እተረጉመዋለሁ — የዛሬ መቶ አመት ይሄ መጸሃፍ ውስጥ ይገባና -ሰያሚው አበበ ከበደ 2011 ዓም ተብሎ ይጻፋል -አስቡበት
እህል=اكل=אוכל=food
ሰካር-ሰካራም- drunk – drunkard =שיכור سكي
Chemistry 101 “ኩሉን ማን ኳለስሽ” the word ኩል = kul=antimony and መኳል = antimonize -Ethiopian wedding song
አኒሜሽን ህይወት ከሚለው ቃል ሊገነባ ይችላል ብለን ብናስብ- ማኸይወት ተብሎ ቢተረጎም በቀላሉ ቋንቋ ውስጥ መግባት ይችላል –አረቦቹ የተረጎሙት ህይወት የሊለውን ቃል ተከትለው ነው [animation=حيوية =ሕየወት)
Electron Configurations and the Periodic Table Check the little STEM Dictionary Here የንጥረ ነገር ሰንጠረጅ የተዋቀረው ተመሳሳይ ቫለንሲ መልክኬሌክትሮን ያላቸው ንጥረ ነግሮች በየዓምዱ እንዲሆኑ ተደርጎ ነው። ለምሳሌ በቫላንሲ ቀፎ ላይ አንድ ኤሌክትሮን ያላቸው በመጀምሪያ ዓምድ ውስጥ ናቸው። ምስሉን እንደሚያሳየው (1) ወይንጠጅ ቀለም ያላቸው ዓምዶች ውስጥ ያሉ ንጥረ ነገሮች መልኬሌክትሮናቸው s-shell or s-ቀፎ ነው በስተግራ መጀመሪያ ያሉት አልካሊ ብረት እና አልካሊምድር ብረትን ያካትታሉ። እነዚህ ንጥረ ነገሮች ውስጥ s-ምሕዋሮች እየተሞሉ ነው። (2) የ 1s ቀፎ የመጀመሪያው s ቀፎ፤ 2p ደግም የመጀመሪያ 2p ቀፎ ነው። 3d የመጀመሪአይ 3d ቀፎ ነው ጥያቄ፡፡የናዮቢዩምን መልኬሌክትሮን ጻፉ What is the electron configuration for the element Niobium? (41) የሚያሳየው 1s2 2s2 2p63s2 3p6 4s2 3d10 4p6 5s2 4d3 <> ጥያቄ፤ የኒኮልን መልኬሌክትሮን ጻፍ ጥያቄ፤ የመጨረሻው የኒኮል ቀፎ ወይም ምሕዋር እዴት እንደተሞላ በስዕል አሳይ፤ መልስ፤ የኤሌክትሮን ከዋነኛ ፀባዮቹ አንዱ በራሱ ዙሪያ መዞር ነው። በራሱ ዙሪያ ሲዞር አንዳንዴ ከቀኝ ወደግራ አንዳንዴ ከግራ ወደ ቀኝ ይዞራል። ይህም ሆኖ የትኛውን አዟዛር እንደያዘ በትክክል ለማወቅ አይቻልም። ይህ ጠባዩ ስፒን ይባላል። ከቀኝ ወደግራ ሲዞር ስፒን-ላይ (spin-up) ይባለል። ከግራ ወደ ቀኝ ሲዞር (ስፒን-ታች)። የመሬትን ቀናዊ አዟዟር ማጤን ወይም በራሷ ዙሪያ መዞሯን ማስታወስ ይጠቅማል 1996 Michael Blaber |