Ethiopian Periodic Table

Posted on : November 15, 2018 |post in : |Comments Off on Ethiopian Periodic Table |

Chemistry Just for smile sake-by Abebe Kebede

ህይድሮጅን ስሙ የመጣው እንደዚህ ነው ΰδωρ (hydōr) = water + γεινομαι (geinomai) = to engender, bring forth⇒ bringing forth water (Greek), named by Antoine Lavoisier in 1793–
እኔ ሳስበው ህይድሮጅን የሚለውን ህዝቡ እንዲገባው ብተረጉመው “የውሃ ብቅል” “በቅለውሃ” “የውሃ ዘር” “ዘረውሃ” እንደ ግዕዝ ደግሞ
“ብቅለማይ” “ዘረማይ” ብዬ እተረጉመዋለሁ — የዛሬ መቶ አመት ይሄ መጸሃፍ ውስጥ ይገባና -ሰያሚው አበበ ከበደ 2011 ዓም ተብሎ ይጻፋል -አስቡበት


እህል=اكل=אוכל=food
ሰካር-ሰካራም- drunk – drunkard =שיכור سكي


Chemistry 101 “ኩሉን ማን ኳለስሽ” the word ኩል = kul=antimony and መኳል = antimonize -Ethiopian wedding song


አኒሜሽን ህይወት ከሚለው ቃል ሊገነባ ይችላል ብለን ብናስብ- ማኸይወት ተብሎ ቢተረጎም በቀላሉ ቋንቋ ውስጥ መግባት ይችላል –አረቦቹ የተረጎሙት ህይወት የሊለውን ቃል ተከትለው ነው [animation=حيوية =ሕየወት)


Electron Configurations and the Periodic Table

Check the little STEM Dictionary Here

የንጥረ ነገር ሰንጠረጅ  የተዋቀረው  ተመሳሳይ ቫለንሲ መልክኬሌክትሮን ያላቸው ንጥረ ነግሮች በየዓምዱ  እንዲሆኑ ተደርጎ ነው። ለምሳሌ በቫላንሲ ቀፎ ላይ አንድ ኤሌክትሮን ያላቸው በመጀምሪያ ዓምድ ውስጥ ናቸው። ምስሉን እንደሚያሳየው

(1) ወይንጠጅ ቀለም  ያላቸው ዓምዶች ውስጥ ያሉ ንጥረ ነገሮች መልኬሌክትሮናቸው s-shell or s-ቀፎ ነው
(2) ቢጫ ቀልም ያላቸው ዓምዶች ውስጥ ያሉ ንጥረ ነገሮች መልኬሌክትሮናቸው  d-shell or d-ቀፎ ነው
(3)አረጓዴ ቀልም ያላቸው ዓምዶች ውስጥ ያሉ ንጥረ ነገሮች መልኬሌክትሮናቸው  p-shell or p-ቀፎ ነው
(4)ሰማያዊ ቀልም ያላቸው ዓምዶች ውስጥ ያሉ ንጥረ ነገሮች መልኬሌክትሮናቸው  4f ወይም 5f-shell or 4 ወይም 5-ቀፎ ነው

በስተግራ መጀመሪያ ያሉት አልካሊ ብረት እና አልካሊምድር ብረትን ያካትታሉ። እነዚህ ንጥረ ነገሮች ውስጥ s-ምሕዋሮች  እየተሞሉ ነው።
በስተቀኝ መጨረሻ ያሉት  6 ንጥረ ነገሮች  ውስጥ የ p-ምሕዋሮች እያተሞሉ ነው።
በመካክል ያሉት ብጫ ዓምዶች ወስጥ ያሉት ተሸጋጋሪ ንጥረ ነገሮች ይባላሉ።  እናዚህ ንጥረ ነገሮች ውስጥ d-ምሕዋሮች እየተሞሉ ነው። ከነዚህ በታች  ያሉት ብሁለት ረድፍና በ14 ዓምዶች ያሉት ንጥረ ነገሮች ናቸው።  እነዚህ ንጥረ ነገሮች ውስጥ f-ምሕዋሮች እየተሞሉ ነው።
ማስታወሻዎች
(1)  2, 6, 10 and 14 የሚባሉት ቁጥሮች የሚያሳዮት  s(l=0), p(l=1), d(l=2) and (l=3)ምህዋሮች ምን ያህል ኤሌክትሮኖች እንዳሚይዙ ነው ይህውም የs-ምሕዋር 2 ፤ የpመሕዋር 6፤ የd ምሕዋር 10 እና የf ምሕዋር 14  ኤሌክትሮኖች  ይይዛሉ። እዚህ ላይ  l የአዚሙጥ ኳንቱም ቁጥር ይባላል።<>

(2) የ 1s  ቀፎ  የመጀመሪያው s ቀፎ፤  2p ደግም የመጀመሪያ 2p ቀፎ ነው። 3d የመጀመሪአይ 3d ቀፎ ነው
(3) n ዋና ቀፎዎችን የሚቆጥር ድፍን ቁጥር ነው።  ለማንኛውም የ n ዋጋ ብዙ ምሕዋሮች ብሎም ቀፎዎች ሊኖሩ ይችላሉ።

ጥያቄ፡፡የናዮቢዩምን መልኬሌክትሮን ጻፉ
መልስ፡፤  ናዮቢዩም 41 ኤሌክትሮኖች ኣሉት

What is the electron configuration for the element Niobium? (41)
የናዮቢዩም መልኬሌክትሮን 1s2 2s2 2p6 3s2 3p6 4s2 3d10 4p65s1 4d4 ነው። ነገር ግን 5s እና 4d የተቀራረቡ ኃይለ ደረጃዎች በመሆናቸው እርገጠኛው መልኬሌክትሮን

የሚያሳየው 1s2 2s2 2p63s2 3p6 4s2 3d10 4p6 5s2 4d3 <>

ጥያቄ፤ የኒኮልን መልኬሌክትሮን  ጻፍ
መልስ፡ ኒኮል 28 ኤሌክትሮኖች ኣሉት ስለዚህ  የኒኮል መልኬሌክትሮን  1s2 2s2 2p6 3s2 3p6 4s2 3d8ጥያቄ፤  የኒኮል መልኬሌክትሮንን አርጎንን መሰረት በማድረግ ጻፍ
መልስ፡ [Ar] 4s2 3d8

ጥያቄ፤ የመጨረሻው የኒኮል ቀፎ ወይም ምሕዋር  እዴት እንደተሞላ በስዕል አሳይ፤

መልስ፤ የኤሌክትሮን ከዋነኛ ፀባዮቹ አንዱ በራሱ ዙሪያ መዞር ነው።  በራሱ ዙሪያ ሲዞር አንዳንዴ ከቀኝ ወደግራ አንዳንዴ ከግራ ወደ ቀኝ  ይዞራል። ይህም ሆኖ የትኛውን አዟዛር እንደያዘ በትክክል ለማወቅ አይቻልም።  ይህ ጠባዩ  ስፒን ይባላል።  ከቀኝ ወደግራ ሲዞር  ስፒን-ላይ (spin-up) ይባለል። ከግራ ወደ ቀኝ ሲዞር (ስፒን-ታች)። የመሬትን ቀናዊ  አዟዟር ማጤን ወይም በራሷ ዙሪያ መዞሯን ማስታወስ ይጠቅማል


1996 Michael Blaber


Theme Designed Bymarksitbd