Message to Students
Posted on : August 14, 2018 | post in : General Knowledge |Comments Off on Message to Students |
ለኢትዮጵያ ተማሪዎች በሙሉ ከአቶ አበበ ከበደ
እንድምን ውላችሁ አድራችኋል እኔ ቸሩ አምላካችን ይመስገን ደህና ነኝ – ይህንን መልክት በጥሞና አንብቡት-ባሁኑ ጊዜ በሃግራችን ብዙ ከባድ ስራዎች አሉ አናንተ ትምህርታችሁን ስትምሩ ለነዚህ ከባድ ስራዎች የሚኖራችሁን ሚና በማሰብ መሆን አለበት ይህን ልታደርጉ የምትችሉት እናንተ በ ሰውናታችሁና በአ ዕምሯችሁ ስትጎለብቱ ነው ስለዚህ ከሚክተሉት አደጋ ሊጥሏችህ ከሚችሉ ነገሮች አደርጉ ወይም ተቆጠቡ (ለሴቶችም ለውንዶችም)- ጓደኛህን ከራስህ በላይ አክብረው
- ጎሳን ሃይማኖትን የሚመለከቱ ሙግት ውስጥ አትግባ
- ስውነትህንና አዕምሮህን ከሚጎዱ ነገሮች ተቆጠብ ጫት አትቃም ሲጃራ አታጭስ
- ሰውነትህን በስፖርት አዳብር
- ሴቶችን አትድፈር እንደ እህትህ እንደናትህ አክብራቸው
- ከጥናትና ከጫወታ የተረፍ ጊዜህን በበጎ ፈቃደኝነት አሳልፈው
- በጥናትህ ትጋ አንብብ አንብብ መርምር አጣራ
- ሃሳብህ ከፍተኛ ትምህርት መማር ከሆነ ማርክህ ከ 3.5 በላይ መሆን አለበት ስለዚህ ማንኛውንም ኮርስ ቢሰለችህም በደንብ አጥንተህ ኤ ማግኘት አለብህ
- ምክር ሲአስፈልግህ ምክር ከሚገኝበት ከቅርብ ዘመድ ከምታምነው ጓደኛ ጠይቅ
- አሉባልታ ውስጥ ምንም ለውጥ የማታመጣበት ጉዳይ ውስጥ አትግባ
- ፌስ ቡክህ ውስጥ የማታቀውን ሰው አታስገባ ወስላታ ሾካካ አድመኛ አኳኋን ካለው ሰው ሽሽ እንደዚህ አይነት ጓደና ካደረግህ ኤፍቢአይ ኢንተርፖል የሚባለው ሁሉ ይከታተልሃል – ይሄ ቀልድ አደለም ተጠንቀቅ
- የምነት ሰው ከሆንክ እምነትህን አጠንክር ግን ያንተ ሃይማኖት ከማንም እንደባይበልጥ እወቅ
ኡኡኡ የንጉስ ያለህ፡
አይ የኔ ወገኖች መቼ ነው የምትማሩት ? እስቲ አካባቢያችሁ የሚሆነውን እዩት – አሁን ከሃምሌ ጀምሮ አሜሪካኖች አንዴ በሰደድ እሳት እንዴ በአውሎ ንፋስ እየተደበደቡ ነው ልብ ብላችሁ ይህንን እዩ- ይህንን ቁጣ ለመከላከልና በሱ ሳቢያ የጠፋውን ንብረት ለመተካት የተጎዳውን ህዝባቸውን መልሶ ለማቋቁም የሚያደርጉትን ጥረት እዩ – ከህፃን ልጅ አንስቶ እስከ ሽማግሌ -ከደሃ አንስቶ እስከ ሃብታም- ከትንሽ ድርጅት አንስቶ እስክ ትልቁ ድርጅት- ሲረባርቡ ታያላችሁ- ኢትዮጵያ ውስጥ ልክ እንደነሱ ያሉ ችግሮች ሞልተዋል ረሃብ ድህንት በሽታ የውሃ እጥረት የአካባቢ መውደም የትምርት ቤቶች መደህየት ምን አለፋችሁ እትዮጵያና ህዝቦቿ ለአመታት ከትውልድ ትውልድ እየላሸቀች ነው -ርብርቡ የታል ? USAID ና የተባበሩት መንግስታት መፍትሄ እንዲሰጡ ነው የምትጠብቁት ? ውስኪ እንደዉሃ ይጠጣል ከፓሪስ ከአዲስ አበባ ክትፎ ይታዘዛል ማርሴዲስ ይነዳል ብር እንደዉሃ ይፈሳል ለልደት ድል ያለ ድግስ ይደገሳል አዲስ አበባ አራዳ ወጥታችሁ ጉድ እዩ- ዲሲ ሄዳችሁ ፓሪስ ሄዳችህ ጉዳችሁን እዩ- ችግርን ለማስወገድ ርብርቡ የታል ? ችግር ዛሬ ከልተፈታ ነገ ሁለት እጥፍ ይሆናል ተነገ ወዲያ አራት እጥፍ ይሆናል -ዝም ብሎ USAID ና የተባበሩት መንግስታት አይጠበቁም – ከአንድ ቀን በፊት ስለ መጽሃፍ ጉዳይ ሃሳብ ልውውጥ ላይ አንደ ወዳጅ USAID ሄደህ አመልክት አለኝ- ሳስበው እኔ ምን ሆኜ ነው USAID ሄጄ አቤት የምልበት ምክንያት ? እጄ ተቆርጧል የአዕምሮ በሽታ አለብኝ ? እሱስ ቢሆን ምን ሆኗል ? ኢትዮጵያ የሚባል ራሱን የቻለ ሕብረተ ስብ አለ -ይሄ ሕብረተሰብ ፋይዳ የሌለው ዋጋ የሌለው ቡቱቶ ለባሽ በሽተኛ ለማኝ ነው ማለት ነው ? በዚህ ምክንያት ያልተወለደውን ገዳዩን ፈረንጅ በእምብርክኩ እየሄደ መለመን አለበት ማለት ነው ? ይሄ ኢትዮጵያዊ አበበ ከበደ የሚባለው እያለ አይሆንም አንለምንም የውጭ እርዳታ ራሳችን እናበጀዋለን -በየሰፈሩ በየጓዳው በየስራቻው ቁጭ ብለን ይህ ይሆናል ያ አይሆንም እያልን ግዜ የምናባክን ሰዎች ተነስትን መስራት አለብን -ልንሰራ የምንችላቸውን ትናንሽ ነገሮች እየመረጥን መስራት እንደየስራው አይነት ራሳችንን ማሰባሰብ ሃሳብ ተቀያየሮ ስራ ላይ ሊውሉ የሚችሉ ነግሮችን መርጦ ስራ ላይ ማዋል – ወሬ በቃ- ከዚህ ጽሁፍ ቀጥሎ ልንሳተፍባቸው የምንችል ውጥኖች ይቀርባሉ የሚስማማችሁን እየመረጣችሁ እርዳታችሁን ለግሱ – እነዚህን ውጥኖች ለምታውቋቸው ሁሉ አስተላልፉ– በትዕግስት ከተሰራ ሁሉም ይሳካል —— ይህ ጽሁፍ ለኢትዮጵያውያን ብቻ ነው የተጻፈው በአማርኛ ነው አማርኛን የሚናገሩ ኢትዮጵያውያን ብቻ ናቸው —ሚስጥር ነው – አማርኛ የማይችል ካለ በጉግል ተርጉም በሉት
Comments are closed.